የአክስዮን ማህበሩ ስም: ሲንቄ ባንክ አ.ማ               የአክስዮን ማህበሩ ዓይነት: የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ የአክስዮን ማህበር
የተፈረመ ካፒታል: 15,000,000,000.00            የባንኩ ምዝገባ ቁጥር: LBB/MT/024/2021
የተከፈለ ካፒታል: 8,009,237,046.00                የአክስዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ: አዲስ አበባ: ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08
                          ለሲንቄ ባንክ አ.ማ ባለአክስዮኖች የተደረገ የስብሰባ ጥሪ
የሲንቄ ባንክ አ.ማ 4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ዓ/ም አንቀጽ 366(2)፣ 370፣ 371፣ 372፣393/3 እና 394(2) እንዲሁም በተሸሻለዉ የባንኩ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 23(2) እና 23 (3.4) መሰረት ቅዳሜ ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል ባለአክስዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚካሄድ በመሆኑ ባለአክስዮኖች በተባለዉ ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ተግኝታችሁ በጉባዔዉ ላይ እንዲትሳተፉ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪዉን ያቀርባል፡፡
የ4ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
1. የጉባዔዉን ድምጽ ቆጣሪዎችን መሰየም፣
2. የጉባዔዉ ምልዓተ ጉባዔ መሟላቱን ማረጋገጥ፣
3. የጉባዔዉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
4. አዳዲስ ባለአክሲዮኖችን መቀበል እና ይህ 4ኛው መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ከመካሄዱ በፊት የተፈጸሙ የአክሲዮን ዝውውሮችን ተቀብሎ ማጽደቅ፣
5. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጥቆማ እና ምርጫ አሰራር ደንብ ሰነድ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
6. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ፣
7. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ምርጫ ማከናወን፣
8. የጉባዔዉን ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ ናቸዉ፡፡
ማሳሰቢያ፡- 
 • በጉባዔዉ ላይ ለመሳተፍ የምትመጡ ባለአክስዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ እና ህጋዊ መታወቂያ/ፓስፖርት ዋናዉን ከአንድ ቅጂ ጋር ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባችሁዋል፡፡
 • በጉባዔዉ ላይ በግንባር መገኘት የማይችሉ ባለአክስኖች በተወካያቸዉ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ዉክልናዉ በባንኩ ዋና መ/ቤት ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ኦዳ ታዎር 7ኛ ፎቅ ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ፎርም ከሶስት (3) ቀን ቀደም ብሎ በመሙላት  ወይም ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ የመንግስት አካል ፊት የተረጋገጠ የዉክልና ሰነድ እና ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ እና ህጋዊ መታወቂያ/ፓስፖርት ዋናዉን ከአንድ ቅጂ ጋር ይዘዉ በመቅረብ በጉባዔዉ ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ሲንቄ ባንክ አ.ማ
Share

Name

Job Title

Related Posts

 • ለሲንቄ ባንክ አ.ማ ባለአክስዮኖች የተደረገ የስብሰባ ጥሪ

  የአክስዮን ማህበሩ ስም: ሲንቄ ባንክ አ.ማ               የአክስዮን ማህበሩ ዓይነት: የባንክ [...]

 • Waamicha Walga’ii Abbootii Aksiyoonaa W.A Baankii Siinqeetiif Taasifame

  Maqaa Dhaabbatichaa : W.A Baankii Siinqee       Gosa Hojii Dhaabbatichi Irratti Bobba’e : Tajaajila Baankii [...]

 • Siinqee Bank Organizes Iftar Dinner Cerimony for Its Customers

  Siinqee Bank Organizes Iftar Dinner Cerimony for Its Customers Siinqee Bank, on Friday 15th of May [...]