Media
ለሲንቄ ባንክ አ.ማ ባለአክስዮኖች የተደረገ የስብሰባ ጥሪ ማስታወቂያ
ሲንቄ ባንክ አ.ማ 5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የንግድ ህግ አዋጅ ቁጥር 1243/2013 ዓ/ም አንቀጽ 366(2)፣ 370፣ 371፣ 372፣ 393/1 እና 394፣ በተሸሻለዉ የባንኩ የመመስረቻ ጽሁፍ አንቀጽ 17/1 እና 7፣ 19/1 እና 3 እንዲሁም 23 መሰረት ቅዳሜ ታህሳስ 5 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ጀምሮ በአዲስ አበባ፣ ኢትዮጲያ ስካይ ላይት ሆቴል ባለአክስዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት የሚካሄድ በመሆኑ ባለአክስዮኖች በተባለዉ ቀን፣ ሰዓት እና ቦታ ተግኝታችዉ በጉባዔዉ ላይ እንድትሳተፉ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ በአክብሮት ጥሪዉን ያቀርባል፡፡
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የንግድ ህግ አንቀጽ 371 መሰረት ባንኩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች
የአክስዮን ማህበሩ ስም:- ሲንቄ ባንክ አ.ማ
የአክስዮን ማህበሩ ዓይነት:- የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ የአክስዮን ማህበር
የተፈረመ ካፒታል (ዋና ገንዘብ):- ብር 15,000,000,000.00
የባንኩ ምዝገባ ቁጥር:_ LBB/MT/024/2021
የተከፈለ ካፒታል (ዋና ገንዘብ):- ብር 8,009,237,046.00
የአክስዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ:- አዲስ አበባ፣ ቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 08
የ5ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች
- የጉባኤዉ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.አ.አ. የ2023/24 የሥራ ዘመን የዳይሬክተሮች ቦርድ አማታዊ የስራ ክንዉን ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.አ.አ. የ2023/24 የሥራ ዘመን የባንኩ የዉጭ ኦዲተሮችን ዓማታዊ የሂሳብ ሪፖርት ማዳመጥ እና ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.አ.አ. የ2023/24 የሥራ ዘመን የትርፍ ድልድል እና አከፋፈልን በተመለከተ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- እ.አ.አ. የ2024/25 የሥራ ዘመን የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ወርሃዊ አበል እና 2023/24 የሥራ ዘመን ዓመታዊ የሥራ ድካም ዋጋ ክፍያ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- የባንኩ የዉጭ ኦዲተሮችን ሹመት መርምሮ ማጽደቅ እና የስራ ድካም ዋጋቸዉ ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
- የሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ ለመቋቋም የቀረበ ፕሮፖዛል/የዉሳኔ ሀሳብ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣
- የሲንቄ ኢንቨስትመንት ባንክ ለመቋቋም የቀረበ የመመስረቻ ጽሁፍ ላይ ተወያይቶ ማጽደቅ፣ እና
- የ5ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ-ጉባዔ ማጽደቅ ናቸዉ፡፡
ማሳሰቢያ፡–
- ጉባዔዉ ላይ ለመሳተፍ የምትመጡ ማንኛዉም ባለአክስዮኖች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ እና ህጋዊ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንገፈቃድ እና የብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ዋናዉን ከአንድ ቅጂ ጋር ይዘዉ መቅረብ ይጠበቅባችሁዋል፡፡
- በጉባዔዉ ላይ በግንባር መገኘት የማይችሉ ባለአክስኖች በተወካያቸዉ አማካኝነት መሳተፍ ይችላሉ፡፡ ዉክልናዉ በባንኩ ዋና መ/ቤት ጆሴፍ ቲቶ መንገድ ኦዳ ታዎር 7ኛ ፎቅ ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች ለዚሁ አላማ በተዘጋጀ ፎርም ከሶስት (3) ቀን ቀደም ብሎ በመሙላት ወይም ዉል ለማዋዋል ሥልጣን በተሰጠዉ የመንግስት አካል ፊት የተረጋገጠ የዉክልና ሰነድ ይዘዉ በመቅረብ በጉባዔዉ ላይ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እየገለጽን በብሄራዊ ባንክ መመሪያ SBB/91/2024 አንቀጽ 20.3 መሰረት የትኛዉም የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት እና የባንኩ ሰራተኞች ዋና ስራ አስፈጸሚ/ፕሬዝዳንት እና ምክትል ዋና ስራ አስፈጻሚዎች/ፕሬዝዳንቶች ጭምር ዉክልና መቀበል የማይችሉ መሆኑን በአክብሮት እየገለጽን፣
- ማንኛዉም የጉባዬ ተሳታፊዎች ማንነታችሁን የሚገልጽ የታደሰ እና ህጋዊ የቀበሌ የነዋሪነት መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጀ ፈቃድ እና የብሄራዊ ዲጅታል መታወቂያ ዋናዉን ከአንድ ቅጂ ጋር ይዛችዉ እንድትቀርቡ በአክብሮት እንገልጻለን፡፡
የዳይሬክተሮች ቦርድ
ሲንቄ ባንክ አ.ማ
Name







